የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ
11 Aug 2021
admin
የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ዋና የስራ ሂደት፡-ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳነቱ ሆኖ ይህ ስራ ሂደት የሚመራው በምክትል ፕሬዝዳነቱ ወይም በስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ይፈፅማል፡፡
- የስራ ሂደቱን ይመራል ፣ይቆጣጠራል ፣ይከታተላል
- የስራ ሂደቱን ሳምንታዊ፣ወራዊ፣የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት እና የዓመታዊ ዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
- የስራ ሂደቱን ሳምንታዊ፣ወራዊ፣የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት እና የዓመታዊ ዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሀላፊ ያቀርባል፡፡
- በስሩ ያሉ ሰራተኞች ሳምንታዊ፣ወራዊ፣የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት እና የዓመታዊ ዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ ይሞላል የአፈፃፀም ሪፖርትንም ተቀብሎ ያጠናቅራል ግብረመልስም ይሰጣል፡፡
- የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ የስራ ሂደትን በሀላፊነት ይመራል፡፡
- ለስራሂደቱ የሚያስፈልጉ ማቴርያሎችን የግዥ ዕቅድ ለሚመለከተው ሀላፊ ያቀርባል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
- በስሩ ያሉ ሰራተኞችን የመራል የከታተላል፡፡
- እራሱን ለለውጥ ሥራ ያዘጋጃል፡፡
- የስራ ሂደቱ ባለሙያዎች የተገልጋይ አቤቱታዎችን መሰረት አድርገው መርምረው የሚያቀባቸውን ጉዳዬች ተገቢው ምላሽ በራሱ ወይም በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ በኩል እንዲፈታ ያደርጋል፡፡
- የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ወይም የበላይ ሀላፊ የሚሰጣቸውን ተጨማሪ ተግባራት ይፈፅማል፡፡