በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በከተማው ምክር ቤት ሰብሳቢነት የምክክር መድረክ ተካሄደ
በሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት በከተማው ምክር ቤት ሰብሳቢነት ሶስቱ የፍትህ አካላት ማለትም ፍርድ ቤት ;ዐ/ህግ ና ፖሊስ በምክር ቤት አፈጉኤ ሰብሳቢነት አገልግሎት አሰጣጣቸውን በተመለከተ ህብረተሰቡ ምን አይነት አውንታዊ ና አሉታዊ ምላሽ እንዳለው ግብአት ህብረተስቡንና ህብረተስቡን የወከሉ ባለድርሻ አካላትና የሀይማኖት አባቶችን በማወያየት በሶስቱም የፍትህ አካላት ጥሩና የሚበረታቱ አገልግሎት አስጣጥ መኖሩን በውይይቱ ተሳታፊ የነበሩ በመግለጽ ነገር ግን በሶስቱም የፍትህ አካላት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች መኖራቸውን ተሳታፊዎቹ በመጠቆም በተለይም በሀዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ፍ/ቤት ና ፖሊስ ጽ/ቤት በጉልህ የሚታዩ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖሩን በመግለጽ የሚመለከታቸው አካላት ያሉትን ችግሮች በቦታው ደርሰው እንዲያጠሩና የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ አስምረው ተናግርዋል በውይይቱ ወቅት ከተለያዩ ተሳታፊዎች የተገኘውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን እንደ ግበአት በመውሰድ ከተሳታፊው የተነሱ ቅሬታዎችን ታች ድርስ በመውረድ እንደሚፈቱ ቃል በመግባት ውይይቱን አጠቃለዋል::