banner

የፕሬዝዳንቱ መልእክት

የፕሬዝዳንቱ መልእክት

የፕሬዝዳንቱ መልዕክት(massage from The president)

የከተማችን ፍ/ቤቶች በአዲስ መልክ ከተቋቋሙበት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ራሳቸውን በተለያየ ሁኔታ በማደራጀት የፍትሕ ሪፎርሞችን ተግባራዊ በማድረግ ለከተማው ሕብረተሰብ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር በተለይ የፍ/ቤቶችን አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የከተማዋን መልክአ-ምድር በማጥናት ሕብረተሰቡ ከምርት ተግባሩ ሳይፈናቀል አገልግሎት እንዲያገኝ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙርያ እንግልት እና ምልልስ እንዲቀንስ በማሰብ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ በማድረግ ጥራትና ቅልጥፍና እንዲኖር ወሳኝ ሥራ ተከናውኗል፡፡ በአስፈፃሚ እና በፈፃሚ ደረጃ የዕውቀት የክህሎት ክፍተት እንዳይኖር በየጊዜው የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና በመስጠት የባለሙያውና ድጋፍ ሰጪው ግንዛቤ እንዲሻሻል ሥራዎች ተሰርቷል፡፡ የፍ/ቤቶች የመረጃ ሥርዓት እንዲሻሻል ከዚህ በፊት በሰው ይሰጥ የነበረው መረጃ ተቀይሮ በቴክኖሎጂ ዲጂታል ሲስተም እንዲሆን በማድረግ ዘመናዊ የመረጃ ሥርዓት ተፈጥሯል፡፡ የለውጥና የሪፎርም ሥራዎችን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት የፍ/ቤታችን አገልግሎት በካይዘን ለውጥ ሥራ ውስጥ በማስገባት ለፈፃሚ ሠራተኞች የግንዛቤ ማሻሻያ በመስጠት በተወሰኑ ሥራ ክፍሎች የሙከራ ሥራው ተጀምሮ አመርቂ ውጤት ታይቶበታል፡፡ በተጨማሪም የፍ/ቤቶቻችን አገልግሎት እየተሸሻለ እንዲሄድ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን በማረጋገጥ ግብአት የመሰብሰብ ሚናን ከፍ በማድረግ በየጊዜው የባለድርሻ ተሳትፎን በቀጣይነት ተግባራዊ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በመጨረሻም የተሰሩ ሥራዎችን ውጤት ለማወቅና ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የተያዙ ዕቅዶችም ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ በማድረግ አስፈፃሚዎችን እና ፈፃሚዎችን የማበርታታት ሥራ ጊዜያቸውን ጠብቆ ተከናውኗል፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ፍ/ቤታችን በአሁን ወቅት በተሻለ አፈፃፀም ደረጃ መሆናቸውን ተገልጋዮች ምስክርነት የሚሰጡት ጉዳይ ነው፡፡

አቶ ማቴ ማጋኔ

የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት