banner

የሃዋሳ ከተማ ከፍ/ፍ/ቤት ታሪካዊ ዳራ፤ ሥልጣንና ተግባር:

                                                          የፍርድ ቤቱ ታሪካዊ ዳራ

የሀዋሳ ከተማ በከተማ አስተዳደር ስትዋቀር የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የሀዋሳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ግንቦት 1996 ዓ.ም ተቋቁመው ስራ የጀመሩ ሲሆንበወቅቱ ፈ/ቤቶቹ ሲራ የጀመሩት ከቀበሌ በተገኘ አሮጌና ጠባብ ክፍሎች ባሏቻ የግለሰብ ቤቶች ውስጥ ስለነበረ ክፍሎቹ ለችሎት የማይመቹ በመሆናቸው የቆርቆሮ ደሶችን ሰርተን ለችሎትና ለቢሮ እንጠቀም ነበር፡፡የሐዌላ ቱላ የመጀመሪያ ደረጃ ፈ/ቤትም  ሶስተኛው የከተማ ፍ/ቤት ሆኖእንደተቋቋመ በግለሰብ ቤት ኪራይ በጣም ጠባብ በሆኑ ክፍሎች ውስጥ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን በወቅቱ ፍ/ቤቶቹ በሰው ሀይል፣በሎጂሰቲክና በአደረጃጀትም በበቂ ሁኔታ ያልተመሟሉ መሆናቸው የትናንት ትውስታችን ነው፡፡

  ዛሬ ፍ/ቤቶቻችን የሚገኙበትን የራሳቸው የሆነ ምቹ የችሎት አዳራሽያሏቸው ዘመናዊ ሕንፃ ውስጥ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ፡፡በአደረጃጀትም ረገድ በአንድ የከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቡለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቶችና በሰባት ምድብ ችሎቶች ተደራጅተው ሕብረተሰቡ ከእለት ተዕለት ሥራው ሳይለይና ከልማት ሳይሰተጓጎል በመኖሪያ አካባቢው የዳኝነት ተደራሽነትን በሚያረጋግጥ መልኩ አገልግሎት የሚያገኝበት ሁኔታ ተፈጥሯል ፡፡በሰው ሀይልና በሎጅሰቲክ አቅርቦትም ከፍተኛ መሻሻል ታይቷል ፡፡አንድ የከፍተኛ ፍ/ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ ተከፍቶ አገልግሎት እየሰጠ የገኛል፡፡ስለዚህ ዛሬን ከትላንት ስናነፃጽር ዛሬ ላይ በርካታ ለውጦችና ውጤቶች የተመዘገቡ መሆኑንና ከግዜ ወደ ግዜ መሻሻሎች መኖራቸውን ማየት እንችላለን፡፡

 

                                               የሃዋሳ ከተማ ከፍ//ቤት ሥልጣንና ተግባር::

የከተማ ከፍተኛ /ቤት በሀገሪቱ ሕግና ደንብ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከሕብረተሰቡ የሚቀርቡትን ጉዳዮች ተቀብሎ ዳኝነት የሚሰጥና የሚያስፈጽም አካል ሆኖ የሚከተሉትን የዳኝነት ሥልጣን አሉት፡፡

  • በፍትሐብሔርና በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጎችና በሌሎች ሕጎች ውስጥ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲያያቸው የተዘረዘሩት ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን፣
  • በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ሥልጣን ሥር የሚወድቁና በውክልና የተሰጡ ጉዳዮች የማየት ሥልጣን አለው፣
  • አንድ ጉዳይ ከሥሩ ካሉ የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ወደ ሌላ የመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ወይም ወደ ራሱ እንዲዛወር የሚቀርብ ጥያቄን ማየት ሥልጣን አለው፣
  • ከፍተኛ /ቤቶች ከመጀመሪያ ደረጃ /ቤቶች በይግባኝ የሚቀርብለትን ጉዳይ አይቶ የመወሰን ሥልጣን አለው፡፡
  • በመጀመሪያ ደረጃ /ቤት ቀርቦ የፀና የማህበራዊ /ቤት ውሣኔ የማየት ሥልጣን አለው፡፡