banner

የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ

የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ

11 Aug 2021 admin

የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ ዋና የስራ ሂደት-ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳነቱ ሆኖ ይህ ስራ ሂደት የሚመራው በምክትል ፕሬዝዳነቱ ወይም በስራ ሂደት አስተባባሪ ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ይፈፅማል፡፡

  • የስራ ሂደቱን ይመራል ፣ይቆጣጠራል ፣ይከታተላል
  • የስራ ሂደቱን ሳምንታዊ፣ወራዊ፣የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት እና የዓመታዊ ዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
  • የስራ ሂደቱን ሳምንታዊ፣ወራዊ፣የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት እና የዓመታዊ ዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አዘጋጅቶ ለሀላፊ ያቀርባል፡፡
  • በስሩ ያሉ ሰራተኞች ሳምንታዊ፣ወራዊ፣የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት እና የዓመታዊ ዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ ይሞላል የአፈፃፀም ሪፖርትንም ተቀብሎ ያጠናቅራል ግብረመልስም ይሰጣል፡፡
  • የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ የስራ ሂደትን  በሀላፊነት ይመራል፡፡
  • ለስራሂደቱ የሚያስፈልጉ ማቴርያሎችን የግዥ ዕቅድ ለሚመለከተው ሀላፊ ያቀርባል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • በስሩ ያሉ ሰራተኞችን የመራል የከታተላል፡፡
  • እራሱን ለለውጥ ሥራ ያዘጋጃል፡፡
  • የስራ ሂደቱ ባለሙያዎች የተገልጋይ አቤቱታዎችን መሰረት አድርገው መርምረው የሚያቀባቸውን ጉዳዬች ተገቢው ምላሽ በራሱ ወይም  በዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ዘርፍ በኩል እንዲፈታ ያደርጋል፡፡
  • የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ  ወይም የበላይ ሀላፊ የሚሰጣቸውን ተጨማሪ ተግባራት ይፈፅማል፡፡