ለሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰራተኞች ስነምግባርና ጸረሙስናን በተመለከተ አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥታል
10 Aug 2021
admin
![](/sites/default/files/2022-12/Newsp1.png)
ባዛሬው ቀን በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰራተኞች ስነምግባርና ጸረሙስናን በተመለከተ አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰታል በዚህም ስልጠና ላይ ለሙስና መስፋፋት እንደምክኒያት የሚጠቀሱት
- የአገልግሎት ሰጪዎች ሶሻል ሞራል አለመኖር
- በአጭር ለመበልጸግ መፈለግ
- ስግብግብነት ና የመሳሰሉት እንደ ዋና ምክኒያት ይጠቀሳሉ
ስለዚ ሙስናና ብልሰሹ አሰራር ሀገርን እንደሚጎዳ በመረዳት በጋራ መዋጋት እንዳለብ በስልጠናው ለይ ለመግለጽ ተሞክሮአል በመቀጠልም ለጠቃላይ ሰራተኛው ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰታል በዚህም ስልጠና ላይ በአሁኑ ሰአት ህብረተሰቡ ኤች አይ ቪ ኤድስ ያለው ግንዛቤ እየቀነሰ መምጣቱንና ህብረተሰቡ በመዘናጋቱ ምክኒያት በኤች አይ ቪ ኤድስ የሚያዘው ሰው ቁጥረበእጥፍ እየጨመረ መሆኑን በመግለጽ ህብረተሰቡ እራሱን ከአስከፊው በሽታ መጠበቅ እነዳለበት በመጥቀስ ለሰራተኛው ግንዛቤ በማስጨበጥ በተጨማሪም ኤች አይ ቪ ኤድስን መተላለፊያ መንገዶቹንና እንዴት መከላከል እንደምነችል በመግለጽ እንደዚሁም ስለማህጸን በር ካንሰረ ለሰራተኛው ግንዛቤ በመስጠት የእለቱን ስልጠና አጠናቀዋል፡፡