banner

የዳኝነት አስተዳደር ዘርፍ

የዳኝነት አስተዳደር ዘርፍ

11 Aug 2021 admin

የዳኝነት አስተዳደር ዘርፍ የስራ ሂደት፡- ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳነቱ ሆኖ ይህ ዋና የስራ ሂደት የሚመራው በዘርፉ አስተባባሪ ሀላፊ ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ይፈፅማል፡፡

  • የስራ ሂደቱን ይመራል ፣ይቆጣጠራል ፣ይከታተላል
  • የስራ ሂደቱን  የግማሽ  ዓመቱንና  ዓመታዊ  የዉጤት ተኮር የስራ ዕቅድ ያዘጋጃል፡፡
  • የግማሽ ዓመት  እና የዓመት የዳኝነት አካሉን የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈፃፀም  ሪፖርት ያጠናቅራል ለበላይ ሀላፊ ያቀርባል፡፡
  • በስራ ሂደቱ የሚተዳደሩ የዳኝነት አካሉን የዓመት  የውጤት ተኮር ዕቅድ ያፀድቃል ወርሀዊ  ሪፖርት ተረክቦ ያረጋግጣል፡፡
  • የዳኝነት አካሉን ዓመታዊ የስራ አፈፃፀም ይሞላል ለበላይ ኃላፊ ዐቅርቦ ያፀድቃል ፡፡
  • ለስራ ሒደቱ የተመደበውን  ዓመታዊ በጀትና ንረት ይመራል ይቆጣጠራል፡
  • የየዕለተን የችሎት ውሎና የስራ አፈፃፀም  እነዲሁም አካሄድ ይከታተላል ፡፡
  • ለስራሂደቱ የሚያስፈልጉ ማቴርያሎችን የግዥ ዕቅድ ለሚመለከተው ሀላፊ ያቀርባል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
  • ለተዘዋዋሪ ችሎት ዳኞችንና ለስራው ድጋፍ የሚሰጡ ሌሎች ሠራተኞችን ይመድባል፡፡
  • እራሱን ለለውጥ ሥራ ያዘጋጃል፡፡
  • ለምድብ ችሎቶችና ለወረዳና ለከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ድጋፍነ ክትትል ያደርጋል፡፡
  • አገልግሎቱን በማያስተጋጉልና በማይጎዳ ሁኔታ ለዳኞች የዓመት እረፍት ይሰታል አፈፃፀሙን፤ይከታተላል፡፡
  • ከሚመለከታቸው  ሀላፊዎች  የሚሰጡትን  ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል፡፡